እግዚአብሔር መሠረትን መስርቷል፡፡ ይህ መሠረት ደግሞ የእኔን ድነት የሚወክለው ኢየሱስ ነው፡፡ ይህ እውነት ለሁሉ አማኞች በእኩል ደረጃ የሚሰራ እውነት ነው፡፡ ነገር ግን እያንዳንዳችን በዚህ መሠረት ላይ የማነፅ ምርጫ አለን፡፡ ሕንፃዎቹ በምድር ላይ በሚኖረኝ የቆይታ ጊዜ ያሉኝን ሐብቶች (ጊዜ፣ ጉልበት፣ ንብረት) አጠቃቀም የሚወክሉ ናቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስን እንደ ዋና የሕንፃ ተቋራጭ በሕይወቴ ቦታ በመስጠት እነዚህን ሐብቶቼን እንዲጠቀም ብፈቅድለት፣ እርሱ በሐብቶቼ የዘላለም ዋጋ ትርፍ ያለውን ሕንፃ ለመገንባት በእኔ ውስጥ በወርቅ፣ በብርና በከበረ ድንጋይ ያንፃል፡፡ በዚህ ሁኔታ ባልሾመው ግን ሕንፃው በእንጨት፣ በሳር ወይም በአገዳ የተገነባ ይሆናል፡፡

1ቆሮ. 3፡10-15 ‹‹የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሀተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፣ ሌላውም በላዩ ያንፃል፡፡ እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ፡፡ ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረም ድንጋይም በእንጨትም በሳርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል፡፡ ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፣ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል፡፡››

Donate Now